Friday, 18 January 2019

// የስስታሙ ነጋዴ ታሪክ
➖➖➖➖➖➖➖➖

በአንድ ወቅት አንድ ፈጣሪ በ!ሰጠው ጸጋ አመስግኖ የማያውቅ ስስታም ነጋዴ ነበር ከዕለታት አንድ ቀን ለንግድ ስራ ከሄደበት ወደ ቤቱ ሲመለስ 100 የወርቅ ሳንቲም ይጠፋበታል ነጋዴው "100 የወርቅ ሳንቲም ያገኘ ካለ ወረታው ከፋይ
ነኝ እያለ ቢለፈልፍም ሊያገኘው አልቻለም። አንድ ቀን ተስፋ ቆርጦ እቤት ቁጭ ብሎ እያለ አንድ ልብሱ የቆሸሸ ገጽታው የተጎሳቀለ ሰውዬ የነጋዴውን ቤት አንኳኳ በር ተከፍቶ ወደ ሳሎን ቤቱ ሲዘልቀ እንግዳው ሰውዬ የመጣበትን ጉዳይ እንዲህ ሲል አስረዳ ጌታዬ 100 የወርቅ ሳንቲም መንገድ ላይ አግኝቼ ነበር ባለቤቱም እርሶ እንደሆኑ ነው የተነገረኝ ምንም የዕለት ጉርሻ የሌለኝ ድሀ ብሆንም የሰው ንብረት አልመኝም ስለሆነም የወርቅ ሳንቲሞን ይዤሎት መጥቻለሁ አለ የሚሰጠውን ጉርሻ ምን ሊሆን እንደሚችል በልቡ እያሰበ ነጋዴው ይህን ሲሰማ ወረታውን ላለመክፈል በአንዴ ፊቱ ተለዋወጠ አንተ እንዳልከው 100 የወርቅ ሳንቲም ብቻ አይደለም የጠፈብኝ በአጠቃላይ የጠፋብኝ የወርቅ ሳንቲም መጠን 125 ነው ስለዚህ 25 የወርቅ ሳንቲም
አስቀርተክብኛል አሁን ሌላ ጣጣ ሳይከተልህ 25ቱን ሳንቲም መልስልኝ ሲል አስፈራራው ምስኪኑ ሰውዬ ከቅንነት ተነስቶ ያደረገው ነገር ያላሰበው ጣጣ
ስለመጣበት እጅግ ተጨነቀ። "ጌታዬ እኔ ያገኘሁት ይሄ ብቻ ነው ምናልባት ሌላ ቦታ ወድቆ እንዳይሆን በፈጣሪ እምልሎታለው እኔ አልወሰድኩም በማለት ሊያስረዳው ሞከረ ይሁን እንጂ ሀብታሙ ነጋዴ አእምሮ በጥቅም ታውሮ ምንም አይነት የርህራሄ ስሜት ሊያሳይ አልቻለም በዚህም 25 የወርቅ
ሳንቲም ወስዶብኛል በሚል ከሰሰው። ድሀው ሰውዬ ከዳኛ ፊት ቀርቦ እንዲህ ሲል ተከራከረ ክቡር ዳኛ ከ 100 የወርቅ ሳንቲም ውጪ ሌላ ነገር አላገኘሁም አግኝቷል የሚል ምስክር ከተገኘ ግን የሚሰጠኝን ቅጣት በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ሲል ተናገረ  በዚህ ጊዜ ጉዳዩን ይመለከት የነበሩት ዳኛ ጠፋ የተባለው የወርቅ ሳንቲም መጠን ምን ያህል እንደሆነ ቀደም ብሎ መረጃ
ደርሷቸው ስለነበር የሚከተለው ውሳኔ አስተላለፉ ጠፋ የተባለው የወርቅ ሳንቲም 100 ብቻ እንደሆነ መረጃ አለን እርስዎ የተከበሩ ከሳሽ ጠፋብኝ እያሉ ያሉት ደግሞ 125 ነው ስለዚህ 100 የወርቅ ሳንቲም የእርስዎ ሊሆን አይችልም ምናልባት 125 የወርቅ ሳንቲም የወሰደ ሰው እስኪገኝ ድረስ ይጠብቁ አሁን የተገኘው ሳንቲም ግን ትክክለኛ ባለቤቱ እስካልተገኘ ድረስ ላገኘው ሰው እንዲሰጥ ወስንናል የሚል ፍርድ ሰጡ በመጨረሻም ድሀው ሰውዬ ሀብት በሀብት ሆኖ ሲመለስ ስግብግቡ ነጋዴ ደግሞ ባዶ እጁን ለመመለስ ተገደደ።

መልካምነት ለራስ ነው። መልሶ ይከፍላልና!